April 22, 2025

#ስጋት እና #ተስፋ 👉 እስከዘላለሙ እንዳይከሽፍ

‎የያዝነው ትልቅ አላማ ነው፣ ጨዋታ ወይም ቀልድ አይደለም።
‎ በተሰጠው የ30 ቀነ-ገደብ ጥያቄያችን ሙሉ በሙሉ የማይመለስ ከሆነ አጠቃላይ የጤና ባለሙያው ወደ ስራ ማቆም ይገባል።
‎
‎ ቀነ-ገደብ የተሰጠው ታካሚ እና ተገልጋዩ ላይ እንግልት ፣ ሞት እንዳይደርስ መንግስት ጊዜ ወስዶ ህዝቡ ሳይቸገር ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ታስቦበት ነው።
‎
‎በአንዳንዶቻችን የተደቀነው #ስጋት ጤና ባለሙያው ሙሉ በሙሉ ለዚህ የተቀደሰ አላማ ትብብር የማያደርግ ከሆነ ብቻ ነው።
‎
‎#ተስፋው ግን አንድነት ሀይል ነው ፣ ፍርሀትን ማስወገድ እና በአንድነት መቆም እና መንግስት እስከዛው ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል የሚል ነው።
‎
‎ሁሉም ጤና ባለሙያ መሳተፍ አለበት። ይህ የማይሆን ከሆነና በአንዳንድ ራስ ወዳዶች የአሁኑ ጥያቄ የሚኮላሽ ከሆነ - ጥያቄያችን የሚከሽፈው እስከ ዘለዓለሙ ነው።
‎
‎ከተዘረዘሩትን 12 ጥያቄዎች ውጪ ሌላ አላማ ወይም የፖለቲካ አጀንዳ የለንም!
‎
‎22 days to go

All Articles