April 7, 2026

#በአስቸኳይ_እንዲፈታ_እንጠይቃለን!

#በአስቸኳይ_እንዲፈታ_እንጠይቃለን!

የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ መምህር እና የእንጅባራ ሆስፒታል ሐኪም፣ የአጥንት ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት የሆነው ዶ/ር አብርሃም አማረ ቀዶ ህክምና እየሰራ ባለበት ሰዓት ፣ ከቀዶ ህክምና ክፍል(Operation Room) ውስጥ፣ በመንግስት የፀጥታ አካላት ለእስር ከተዳረገ ሳምንት አለፈው።
‎
‎የእስሩን ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዳይወጣ እና በውስጥ ለመጨረስ በሚል ይዘነው የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ሊፈቱት ባለመቻሉ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው በሚል አሁን ይፋ ለማድረግ ተገደናል።
‎
‎120 የማይሞሉ የአጥንት እስፔሻሊስት ባለባት ሀገር ከምንም ነገር ጋር ግንኙነት የሌለውን ሀኪም ከስራ ቦታው ወስዶ ማጎር ለህዝብ፣ ለሀገር አለማሰብ እና ደንታ ቢስነት ነው።
‎
‎ዶ/ር አብረሃም አማረን ማሰር ፤1,000,000 ኢትዮጵያዊያንን ህክምና እንደመንፈግ ይቆጠራል !
‎
‎ሀኪሙን በአስቸኳይ እንድትፈቱት እና ወደ ታካሚዎቹ እንዲመለስ ስንል እንጠይቃለን ። ይበቃል‼️

በአስቸኳይ ፍቱት!

All Articles