Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
በ470 ብር ክልከላ እና በህይወት መስዋዕትነት መካከል ያለችው ኢትዮጵያ!

በ470 ብር ክልከላ እና በህይወት መስዋዕትነት መካከል ያለችው ኢትዮጵያ!

November 28, 2025
አማኑኤል ካሳን በጂንካ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ክፍል በሰራንባቸው ጊዜያት በሙያው ቁርጠኛ እና ለፍትህ የማይደራደር ባለሙያ ሆኖ ነው።
አማን በህይወት ዘመኑ የታገለው ለአንድ ነገር ነበር - ለፍትህ! በሆስፒታሉ ውስጥ ለነርሶች ሊከፈል የሚገባው የ470 ብር የአደጋ ተጋላጭነት አበል (Risk Allowance) ለምን ተከለከለ ብሎ እስከ ክልል ቢሮ ድረስ ተከራክሯል። መልሱ ግን... ዝምታ... እና ...ቢሮክራሲ.. ነበር። የሚገርመው ነገር፣ ያኔ ስርዓቱ ...ተጋላጭ.. አይደለህም ብሎ የ400 ብር መብት የነፈገው ባለሙያ፣ ዛሬ እራሱን አጋልጦ ወገኑን ሲያክም በማርበርግ ቫይረስ ህይወቱን ከፈለ።
ይብሱኑ ሌላ ልብን የሚሰበር ዜና ሰማን፡፡ የአማን ባለቤትም በቫይረሱ ህይወቷ አልፏል። ስርዓቱ የነፈጋቸውን መብት ወደጎን ብለው ህዝብን ሲያገለግሉ የነበሩት እነዚህ ጥንዶች፣ ዛሬ ልጆቻቸውን ለእኛ አደራ ሰጥተው አልፈዋል።
ስርዓቱ ሲበድላቸው፣ እነሱ ግን እስከመጨረሻው እስትንፋስ አገልግለዋል። አሁን ጥያቄው ወደ መንግስት ነው፡-
1. ለሞቱት ክብር ይሰጣቸው ይሆን?
2. ሜዳ ላይ ለቀሩት ለነዚህ ጀግኖች ልጆች የፌደራል እና የክልል መንግስት ምን ያደርጋል?
ይህን ሁሉ ግፍ፣ ይህን ሁሉ መከራ በልጅነት አይኗ የምታየው የነርስ አማን ልጅ ህጻን ሄመን፤ አባቷን ባጣችበት ጋዋን እና ስቴቶስኮፕ ነገ አድጋ "ሀኪም መሆን እፈልጋለሁ" ትል ይሆን?
ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።
More info: https://www.healthvoiceethiopia.com/